arrow_back Back to News • Jun 03, 2026

የተሽከርካሪ ባለቤትነት ስም ዝውውር ቅደም-ተከተል

Source: አልተር | Alter

የተሽከርካሪ ባለቤትነት ስም ዝውውር ቅደም-ተከተል

ደረጃ 1፦ ቅድመ-ዝግጅት እና መነሻ ሰነዶች (ሻጭና ገዢ የሚያዘጋጇቸው)

የተሽከርካሪው ሊብሬ፦ ዋናውን የባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር (ሊብሬ) ማቅረብ።

የመታወቂያ ሰነዶች፦ ሻጭ እና ገዢ ግለሰቦች ከሆኑ የሁለቱም የታደሰ የቀበሌ/የከተማ መታወቂያ ማቅረብ።

የውክልና ሰነድ (አስፈላጊ ከሆነ)፦ ሽያጩን የሚፈጽመው የባለንብረቱ ተወካይ ከሆነ፣ በፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ (ውልና ማስረጃ) የጸደቀ ሕጋዊ ውክልና ማቅረብ።

ፎቶግራፍ፦ የገዢው ስድስት ወር ያልሞላው ሁለት ጉርድ ፎቶግራፍ።

ደረጃ 2፦ የተሽከርካሪ ዋጋ ግምት እና የግብር ሂደቶች

የዋጋ ግምት መቀበል፦ ከተሽከርካሪ እና አሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የተሰጠ የተሽከርካሪ ዋጋ ግምት ሰነድ መቀበል።

የሽያጭ ግብር ክፍያ፦ የተሽከርካሪውን ዋጋ ግምት መሠረት ያደረገ የሽያጭ ግብር ክፍያ መፈጸም።

የግብር ነፃ ማረጋገጫ (ለኮድ 3 ብቻ)፦ ተሽከርካሪው ኮድ 3 (የንግድ/የትርፍ) ከሆነ፣ ከገቢዎች ሚኒስቴር ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የተሰጠ ከግብር ነፃ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰነድ (Clearance) ማቅረብ።

ደረጃ 3፦ ውል ማረጋገጥ እና ማጠቃለያ

የመጀመሪያ ውል ፎርም፦ ሻጭ እና ገዢ በጽሕፈት ቤቱ የተዘጋጀውን የሽያጭ ውል ፎርም በጋራ ሞልተው መፈራረም።

ሕጋዊ ውል ማቅረብ፦ በፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ ኤጀንሲ (ውልና ማስረጃ) የተረጋገጠውንና የጸደቀውን ዋናውን የሽያጭ ውል ማቅረብ።

ማጠቃለያ ቁሳቁሶች እና ክፍያ፦ ለሰነዱ የሚሆን ቴምብር ማቅረብ እና የተወሰነውን የአገልግሎት ክፍያ በመክፈል የባለቤትነት ስም ዝውውሩን ማጠናቀቅ።