arrow_back Back to News • Jun 03, 2026

ክፍል 3፦ የተሽከርካሪ ቴክኒክ ምርመራ ሲደረግ የመጀመሪያው ትኩረት የሚሰጠው

Source: softcover

ክፍል 3፦ የተሽከርካሪ ቴክኒክ ምርመራ ሲደረግ የመጀመሪያው ትኩረት የሚሰጠው
  1. የፍሬን ሥርዓት (Brake System)የእጅ ፍሬን (Hand Brake)፦

     ቢያንስ ሁለት እግሮችን የሚይዝ፣ ሲያዝ የማያፈተልክ፣ እጀታው ብዙ ርቀት የማይጓዝ እና ሜካኒዝሙ በደንብ የሚሠራ መሆን አለበት።የእግር ፍሬን (Foot Brake)፦ * በንፋስ የሚሠራ ከሆነ፦ ከ3-4 ደቂቃ ውስጥ ሙሉ ንፋስ የሚያከማችና የማያስተነፍስ፣ ጌጁ የሚሠራ እና ሁሉንም እግሮች እኩል የሚያቆም መሆን አለበት።በዘይት የሚሠራ ከሆነ፦ ፓምፕ ሳይደረግ (በአንድ ረገጣ) የሚይዝ፣ የዘይት ፍሳሽ የሌለው እና ሲለቀቅ ፍሬን ይዞ የማይቆይ መሆን አለበት。
    
  2. ሜካኒካልና የውስጥ ክፍሎች ፍተሻአረግራጊ ክፍሎች (Suspension)፦

    አሞርዛቶርና ባሌስትራ የተሰበሩ መሆን የለባቸውም።በርና ኮፈን፦ መገጣጠሚያው ያልወላለቀ፣ ውሃ የማያስገባ እና በትክክል የሚቆለፍ።የመስተዋትና መጥረጊያ፦ የፊት መስተዋት የፋብሪካ (Safety glass) ሆኖ ስንጥቅ የሌለው፤ የዝናብ መጥረጊያው በበቂ ፍጥነት ሙሉውን የሚጠርግ መሆን አለበት።መቀመጫዎች (Seats)፦ ያልረገቡና ምቹ የሆኑ፣ የሾፌሩ መቀመጫ የሚስተካከል፣ በሕዝብ ማመላለሻ ወንበር ሥር የነዳጅ ጋን የሌለው።የጎማ ሁኔታ፦ አስተማማኝ የጎማ ጥርስ ያለው፣ ቸርኬው ያልተሰነጠቀ እና በስፔስፊኬሽኑ መሠረት ንፋስ የተሞላበት ($Pressure$)።

  3. የአካባቢ ጥበቃ እና አስገዳጅ የደህንነት መሣሪያዎችየጭስ ሁኔታ፦

    ተሽከርካሪው ብዙ ጭስ ማውጣት የለበትም። ማርሜታው ያልተቀደደና ከፍተኛ ድምፅ የማይሰማ መሆን አለበት። ከተሽከርካሪው የሚወጣው የካርቦን ሞኖኦክሳይድ ($CO$) እና የሃይድሮካርቦን ($HC$) መጠን መታወቅ አለበት።የመከላከያ መሣሪያዎች፦ እያንዳንዱ ተሽከርካሪ የመጀመሪያ ሕክምና መስጫ ሳጥን (ከነመድኃኒቱ)፣ የእሳት አደጋ መከላከያ (አጥፊ)፣ አንጸባራቂ የሶስት ማዕዘን ምልክት፣ ታኮ እና ክሪክ መያዝ ግዴታው ነው።